የማዕከሉ አድራሻ: | ካርታ
በማስታወቂያ ካልተገለፀ በስተቀር፤ኮርሱ የሚካሄድበት ቋንቋ አማርኛና እ,ንግሊዝኛ ነው።: እንግሊዝኛ
እንዴት ኮርስ ለመሳተፍ ወይንም ለማገልገል ማመልከት ይቻላል።
- ለመሳተፍ ያቀዱትን ኮርስ ላይ «ማመልከት»የሚለውን ምልክት በመጫን የማመልከቻውን ቅጽ ያውጡ።
- እባክዎ የኮርሱን መግቢያና በልምምድ ጊዜ እንዲከተሉ የሚጠየቁትን ስርአት በጥንቃቄ ያንብቡ።
- የማመልከችውን ቅጽ ጠቅላላ ሞልተው ያጠናቁና ያስገቡ።በሁሉም ኮርስ ለመሳተፍ ማመልከቻ መሙላት የግድ ያስፈልጋል።
- ምላሽ ጥበቃ፦ሁሉም መጻጻፍ የሚካሄደው በማመልከቻዎ ውስጥ ባቀረቡት ኢሜል አማካኝነት ነው።ከአመልካቾች መብዛት የተነሳ አንዳንዴ እስከ ሁለት ሳምንታት መልሳችን ሊዘገይ ይችላል።
- ኮርሱን እንደሚሳተፉ ካሳወቅኖት በኋላ ፤ቦታዎን ለማረጋገጥ የመሳተፍ ፍላጎትዎን ወዲያውኑ ደግመው ሊያረጋግጡልን ይገባል ።
በኢንተርኔት የሚያስገቡት ማመልከቻ ፤ከእርሶ ኮምፒውተር ወደእኛ ከመላኩ በፊት በሚስጥራዊ አጻጻፍ ይቀየራል።እንደዛም ሆኖ ሙሉ በሙሉ ከተነባቢነት ይድናል ማለት አይደለም።የግል መገለጫዬ በልላ አካል ተነቦ ለደህንነቴ ስጋት ሊፈጥር ይችላል የሚል ፍርሀት ከካለብዎ፤በኢንተርኔት በመላክ ፋንታ የሚታተም ግልባጭ ከ download ላይ አውርደው ይሙሉና ፤በፋክስ ወይንም በፖስታ ቤት ሊልኩልን ይችላሉ።ይህ ሂደቱን በአንድ ወይም ሁለት ሳምንት ሊያጓትተው ይችላል።
በአካባቢዎ የሚገኘውን የነባር ተማሪዎች ድረ-ገጽ ለመጎብኘት here. ይጫኑ። የተጠቃሚ ሚስጢራዊ መግቢያ(ፓስ ዎርድ)ያስፈልጎታል።
ጥያቄ ለመጠየቅ Email: [email protected] ይጠቀሙ።
ሁሉም ኮርሶች የሚካሄዱት በችሮታ ነው።.የኮርሱ ወጭዎች የሚሸፈኑት ከዚህ በፊት ይህን ኮርስ ተካፍለው ጥቅም ባገኙ ነባር ተማሪዎች ሲሆን ፤የሚለግሱትም ችሮታ እነሱ በዚህ ሜዲቴሽን ያገኙትን ጥቅም ሌሎችም እድሉ እንዲደርሳቸው በማሰብ ነው።አሰተማሪዎችም ሆኑ ረዳት አስተማሪዎች በግልጋሎታቸው ምንም አይነት ካሳ አይከፈላቸውም።አስተማሪዎችና ልሎች የኮርሱ አገልጋዮች ፤የሚያገለግሉት ጊዚያቸውን ሰውተው በነፃ ነው። ይህ ሁናቴ የቪፓሳና ትምህርት ከንግድ ጋር ባልተገናኘ ንጹህ መንፈስ እንዲተላለፍ ይረዳል ።
ነባር ተማሪዎች ማለት በመምህር ጎይንካ ወይንም በረዳት አስተማሪዎቻቸው የአስር ቀናት የቪፓሳና ኮርስ ያጠናቀቁ ግለሰቦችን ማለት ነው።
ነባር ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሱት ኮርሶች የነፃ ግልጋሎት ላይ ማበርከት ይችላሉ።
ባለ-ጥንድ ቋንቋዎች ማለት፦ኮርሱ በሁለት አይነት ቋንቋ የሚተሰጥባቸው ኮርሶች ማለት ነው።ሁሉም ተማሪዎች የእለት መመሪያውን የሚወስዱት በሁለቱም ቋንቋ ሲሆን የምሽት መመሪያው ግን እንደ ምርጫዎ በአንደኛው ቋንቋ ይሆናል።
የሜዲቴሽን ኮርሶች በቋሚ ማዕከሎች ወይንም በጊዜያዊ ማዕከሎች ውስጥ ይካሄዳሉ።ሜዲቴሽን ማዕከሎች የተቋቋሙት ሜዲቴሽን ለመለማመጃ ብቻ ሲሆን ፤ኮርሶች አመቱን ሙሉ ይዘወተርባቸዋል።ቋሚ የሜዲቴሽን ማዕከሎች ከመገንባታቸው በፊት ሁሉም ኮርሶች ይካሄዱ የነበሩት እንደ ኀይማኖት ተቋሞች፤ትምህርት ቤቶችና መጠለያ ሜዳዎች የማሳሰሉት ቦታዎች ላይ ነበር። በአሁኑም ወቅት ቢሆን ፤በነባር ተማሪዎች የሜዲቴሽን መእከሎች ባልተገነባባቸው ክልሎች ኮርስ ማካሄድ ካስፈለገ፤በጊዜያዊ ማዕከሎች ውስጥ የ10 ቀናት ኮርሶች ይካሄዳሉ።